Community Support | ለማህበረሰባችን የምንሰጠው ድጋፍ
ተጨማሪ መረጃዎችን ያካተቱ ፍላየሮች ለማንበብ ምስሎቹን ይጫኑ።
Click on the images for informational flyers
በሚግባቡበት ቋንቋ ትርጉም ማግኘት መብትዎ ነው!
Language Access is your right!
በዲሲ ቋንቋ ተደራሽነት ህግ መሠረት፣ ከመንግስት ኤጄንሲዎች እና ቢሮዎች አገልግሎቶችን በሚፈልጉበት ጊዜ፣ እርስዎ በመረጡት ቋንቋ ትርጉም (የጽሁፍ ሰነዶችንም ትርጉም ጨምሮ) የመጠየቅና የማግኘት መብት አልዎት። ይህ መብትዎ ተጥሶ እንደሆነ፣ ለዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ አቤቱታ የማቅረብ መብት አልዎት። ቅሬታዎችን ወይም ሌሎች የቋንቋ ተደራሽነት ፍላጎቶችን እና ጉዳዮችን ለማመልከት እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን ጽ / ቤታችንን ይጎብኙ ወይም ያግኙን!
Under the DC Language Access Act, when seeking services from government agencies and offices, you have the right to request interpretation and translation of all written documents in your preferred language. If you have been denied, you have the right to file a complaint with the DC Office of Human Rights. If you require assistance in filing a complaint or other language access needs and concerns, please visit our office or contact us!
በዲሲ ውስጥ የደሞዝ ስርቆትን/ዝርፊያን ለማጥፋት ይተባበሩ!
Fight Against Wage Theft!
ዲሲ የሚሰሩ ከሆነ የሚከተሉት መብቶዎ ናቸው ፦
በሰዓት ቢያንስ $15 ሊከፈልዎ ይገባል፣ ጉርሻን መሠረት ላደረገ ዝቅተኛ ደሞዝ/ክፍያ፤ በሰዓት $5.00 ያላነሰ መሆን አለበት፡፡ ይህ ዝቅተኛ ደሞዝ/ክፍያ ከሚያገኙት ጉርሻ ጋር ተደምሮ በሰዓት ቢያንስ $15 መድረስ ይኖርበታል ፡፡
የተጨማሪ ሰዓት (ኦቨርታይም) ክፍያ፣ በሳምንት ከ40 ስዓት በላይ ከሠሩ፣ የተጨማሪው ሰዓት (ኦቨርታይም) ክፍያ በ1.5 ተባዝቶ ሊከፈልዎ ይገባል፡፡
ክፍያ ያለው የህመም ፈቃድ ሊኖርዎ ይገባል፡፡
ቀጣሪዎ መብትዎን የማያከብር ከሆነ እንነጋገር! ወደ ወርሃዊ የክፍያ ደረሰኝ (ፔይስታብ) ክሊኒክችን ይምጡ ወይም ይደውሉልን/መልዕክት ይላኩልን። አልያም ደግሞ ዲሲ ጆብስ ዊዝ ጀስቲስ (DC Jobs with Justice) ደህረ-ገጽ ይጎብኙ።
If you work in DC you have a right to:
Make at least $15 per hour The minimum wage for tipped workers is $5, but your tipped earnings in addition to your wages must equal at least $15.
Overtime Pay: Earn 1.5 times your hourly wage for all hours worked over 40 per week
Paid sick days
If your employer is not respecting your rights let's talk! Come to our monthly pay stub clinics or contact us or contact DC Jobs with Justice.
የሊድ መመረዝን ይከላከሉ!
Prevent Lead Poisoning!
ሊድ ለጤና አደገኛ ነው። መረጃዎቻችን እና ድጋፋችን ቤተሰብዎን በሊድ ከመመረዝ እንዴት መከላከል እንደሚችሉ፣ ቤትዎን እንዴት እንደሚያስመርምሩ፣ ስለ ውሃ ምንጭዎ የበለጠ ማወቅ እንዳለቦዎት፣ ከ0-2 ዓመት እድሜ ላይ ያሉ ልጆችዎን ማስመርመር እንዳለቦዎ ይበልጥ ለማወቅ ይረዳዎታል። ለበለጠ መረጃ የዲሲ የአካባቢ እና ኢነርጂ ዲፓርትመንትን ደህረ-ገጽ ይጎብኙ።
Lead is a health risk! Our resources and support will help you to learn how you can keep your family safe from lead poisoning, how to get a home inspection, learn about your water supply and that it is crucial to get your 0-2 year old children tested for lead. Visit Department of Environment and Energy's website for more information.